ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የ110 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ::

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለገጠር ፋይናንስና ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የ110 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሺዴ እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የፐብሊክ ዘርፍ ዳይሬክተር ሚስተር ዲደሪክ ዛምቦን ናቸው።

የስምምነቱ ዋና ዓላማዎች በጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ዘርፎች ለተሰማሩ ዜጎች የፋይናንስ አቅርቦትን በማመቻቸት በመላ ኢትዮጵያ ዘላቂ የግብርና እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ማሳደግ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገንዘቡን ለገጠር የፋይናንስ ተቋማት፣ ለጥቃቅን ፋይናንስ ተቋማት እና ለኅብረት ሥራ ማኅበራት በማስተላለፍ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንደሚያደርግም ተመላክቷል።

ይህ ፕሮጀክት ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ ከሚገኝ የ35.1 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እና የ4.8 ሚሊዮን ዶላር ብድር ጋር ተቀናጅቶ የሚከናወን መሆኑም ተጠቁሟል።

ለዚህም የአውሮፓ ኅብረት የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዚህ ስምምነት መፈረም በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ መካከል ያለውን የቆየና የጠነከረ አጋርነት ይበልጥ የሚያጎለብት መሆኑ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *