ከ100 በላይ አውሮፕላኖችን የታጠቀው የኢትዮጵያ አየር ኃይል

************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለውጡ ሲመጣ አንድ ሄሊኮፕተር ብቻ የነበረው የተቀረው መብረር የማይችል አውሮፕላን ነበር፣ ዛሬ ላይ የተለያየ ስምና ተግባር ያላቸው ከ100 በላይ አውሮፕላኖች ባለቤት ሆኗል ሲሉ አስታወቁ፡፡

ለምንድን ነው ተቋም የምንገነባው? የተባለ እንደሆነ ባንዳ ከማቁሰል አያልፍም፤ ዝግጅቱ ግን ምሰሶውን የሚገዳደሩ ኃይሎች ከመጡ ኢትዮጵያን ለማጽናትና ለማስቀጠል ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ላይ የተሠራው ሥራ የተቋም ግንባታ አካል መሆኑንም አስረድተዋል።

በኢኮኖሚ፣ በተቋማት ግንባታ የማድረግ አቅማችንን የምናሳድገው ኢትዮጵያን የሚያጸኑ ምሰሶዎችን መጠበቅ ግዴታ ስለሆነ ነው ብለዋል።

ከባንዳዎች የበለጠ ሃብት ካላመነጨን በስተቀር በሃብት፣ በሚዲያ፣ በዲፕሎማሲ ምክንያት ጫና ይፈጠራል ሲሉም ገልጸዋል።

መፍትሔው ብቃትን በማጎልበት ጠንክሮ መገኘት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያን መጉዳት የሚፈልጉ ኃይሎች ፋይናንስ ቢደረጉም ኢትዮጵያን የሚያስቆሙበት አንዳች አቅም እንደሌላቸው አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *