በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተግባራዊ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ::

ቢሮው በ100 ቀናት እቅድ ውስጥ ከፍትህ እና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመተባበር በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ነጻ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ተግባራዊ ማድረጉን የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሌሊሴ አህመድ ገለፁ ።

ሴቶች ህጻናት ያለምንም የጥቃት ስጋት እና የተጠናከረ የመረጃ ድጋፍ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማስቻል ረገድ ማዕከሉ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

በተጨማሪም በፍትህ ሥርዓት ውስጥ ለሚያልፉ ህጻናት ሊደረጉ የሚገባቸው የጥበቃ እና እንክብካቤ ሥራዎችም እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ሴቶችን ከተረጂነት ለማውጣት ለ50 ሴቶች ለየአንዳንዳቸው ከብር 100ሺ እስከ 600ሺ ድረስ የብድር ምችችት እንዲያገኙ እና በተለያዩ የንግድ ስራዎች ተሰማርተው እንዲሰሩ በማድረግ መቻሉንም ኃላፊዋ አስረድተዋል።

የህጻናት ማቆያ ማዕከሉንም በማቴሪያል በማደራጀት እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ የቁሳቁስ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈንም በርካታ ጥረት እየተደረጉ መሆኑን አስረድተዋል።

የተቋሙን ሰራተኛ የፋይዳ መታወቂያ እንዲወስድ በማድረግ በኩሉ ሁሉም ሰራተኛ እንዲወስድ ማድረግ መቻሉን እና የእቅዱን ማሳካት መቻሉን ፣የ5ሚሊዮን ኢትዮኮደርስ ስልጠና ከ48% በላይ ሰራተኛው እንዲወሰወድ ማድረግ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *