7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሀዊ፣ ሰላሚዊና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ::

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ ፣ ዴሞክራሲያዊ ፣ ተዓማኒነትና ቅቡልነት ያለው እንዲሆን የወጣቶች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርጫፍ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሁዲን አብዱረህማን ገልፀዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የወጣቱን የመልማትና በነፃነት ሀሳቡን የመግለፅ እንዲሁም የመናገር እድሉን ከፍ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ አቶ ሙሀዲን ጠቁመዋል።

አቶ ሙሀዲን አያይዘውም ወጣቶች ሀገራዊ ምርጫው ፍፁም ዲሞክራሲያዊ፣ ነፃና ገለልተኛ እንዲሁም ሰላማዊ ሆኖ እንድጠናቀቅ ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ወጣቶች በቅደመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅትና በድህረ ምርጫ በንቃት መሳተፍ ይገባቸዋል በማለት ኃላፊው መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *