የአፍሪካ ቀንድ የወጣቶች ፎረም በድሬዳዋ አስተዳደር ተካሂዷል::

” ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና የአየር ንብረት ለዉጥ መፍትሔዎች ወጣት መር ጥረቶችን ማበረታታት ” በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር አዘጋጅነት የአፍሪካ ቀንድ የወጣቶች ፎረም በዛሬው እለት ተጀምሯል ።

በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ፎረሙ ቀጠናዊ ሰላም ከማምጣት በዘለለ ለድሬዳዋ ወጣቶች እንደ ጥሩ መነሻ ከመሆኑም በላይ ወጣቱ እርስ በርስ የሚግባቡበትን ዕድል እንደሚፈጥርም አስታውቀዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ወጣቶች በዚህ መልኩ መሰባሰባቸዉ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልፀዉ የኢትዮጵያን ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ፎረሙ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ ተናግረዋል ።

የድሬዳዋ የወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወጣት ሃሚድ አብደላ በበኩላቸዉ ፎረሙ በዋነኝነት በአየር ንብረት ለዉጥና በቀጠናዊ ሰላም የሚያጠነጥን መሆኑን ገልፆ በተለይ ድሬዳዋ ሰላም መሆኗን ለሌሎች ሀገራት የምናሳይበት መንገድ ይሆናልም ብለዋል ።

በፎረሙ ላይም ከጂቡቲ ፣ ከሶማሊያ ፣ ከሶማሌላንድ ፣ ከደቡብ ሱዳን ፣ የኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ፣ የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ እና ፕሬዝዳንት ፣ የየክልሉ የወጣት ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *