በድሬዳዋ አስተዳደር ‎በዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ከ5ሺ በላይ ሄክታር መሬት ማልማት ተችሏል::

በአስተዳደሩ”‎የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ለግብርና ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የነበረው የ2018 የተፋሰስ ልማት የመዝጊያ እና የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

‎በመርሃግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጅሀር፤ ‎አስተዳደሩ ለተፋሰስ ልማት ስራ ትኩረት በመስጠት ተፈጥሮን ወደነበረበት ለመመለስ ባከናወነው ተግባር ውጤት ማስመዝገቡንም ተናግረዋል።

የተፋሰስ ልማት ‎ስራዎች ሀገሪቱ የጀመረችውን ከተረጅነት የማላቀቅና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የሚደረገውን ጥረት በማሳካት በኩል ድርሻው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ክቡር ከንቲባው ‎አክለውም ለገጠሩ ሽግግር መሠረት በመጣል ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ የብልጽግና ሽግግር ስኬታማነት በእጅጉ የሚያግዝ መሆኑን እና በቀጣይም አንድነታችንን በማጠናከር ለህዝብ በሚጠቅሙ መሰል የልማት ስራዎች ላይ በጋራ ልንሰራ ይገባልም ብለዋል።

‎የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ውሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላም በበኩላቸው፤ የተፋሰስ ልማት ላለፉት በርካታ አመታት ሲሰራ የቆየና ለአርሶ አርብቶ አደሩ ባህል እየሆነ የመጣ መሆኑን አስረድተዋል።

‎በዘንድሮ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ንቅናቄም 41,149 ሺህ ህዝብ በሰው ሀይል በማሳተፍ በገንዘብ ሲተመን 900,506,100 ማዳን መቻሉን ገልፀዋል።

‎በዘንድሮ በተቀናጀ ተፋሰስ ሥራ ከ5,328 ሄክታር መሬት በላይ መልማቱን በዚህም በ3.6 የመሬት መራቆት ችግርን መቅረፍ መቻሉን ገልጸዋል።

‎የአፈር መሸርሸር፣ የማህበረሰቡ የጎርፍ ተጋላጭነት መጨመር እና ሌሎች ተግዳሮቶችን ለመፍታት ህብረተሰቡን ያሳተፈ የተፈጥሮ ሀብት ጥብቃ ሥራ በመስራት 46,737 ቶን ለም አፈር ማዳን መቻሉንም ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩም በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የላቀ አፈጻጸም ለነበራቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

‎በመርሃ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብር አብዲ ሙክታር፣ ምክትል ከንቲባ ክብር አቶ ሀርቢ ብህ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ ሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *