በድሬዳዋ አስተዳደር የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እና የ 5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ተገመገመ::

በድሬዳዋ አስተዳደር የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እንዲሁም ደግሞ የ 5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ምዝገባ እየተካሄደ ሲሆን እነዚህም ምዝገባዎች ያሉባቸው ደረጃ በዛሬው ተገምግሟል ።

ከዲጂታል መታወቂያ ጋር ተያይዞ በድሬዳዋ አስተዳደር ያለው አፈፃፀም ጥሩ ቢሆንም ነገር ግን በቀጣይ 5 ወራት 133 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ማስመዝገብ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀርቢ ቡህ ተናግረዋል ።

አቶ ሀርቢ አክለውም ከ 5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ጋር ተያይዞ በድሬዳዋ አስተዳደር በቀጣይ ሶስት አመታት ውስጥ 37 ሺህ ነዋሪዎች መመዝገብ እንዳለባቸውና እስካሁን ድረስም ባለው መረጃም ከ 17 ሺህ በላይ ወጣቶች መመዝገባቸውን ተናግረው በቀጣይ 5 ወራትም ከ 19 እስከ 20 ሺህ ወጣቶች መመዝገብ እንዳለባቸውም ነው አቶ ሀርቢ ቡህ በእለቱ ያስታወቁት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *