የፋይዳ መታወቂያ እንደስሙ ፋይዳው የላቀ በመሆኑ ምዝገባውን ያላከናወኑ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ምዝገባ በማከናወን የመታወቂያው ባለቤት እንዲሆኑ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ም/ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ጥሪ አቀረቡ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት እንዲሆኑ በቅንጅትና በርብርብ እየተሰራ እንደሚገኝ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ገልፀዋል።

በአስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም በአጠቃላይ ከአምስት መቶ ሶስት ሺ (5 መቶ 3 ሺ) በላይ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ መካሄዱን ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ጠቁመው በ2018 ደግሞ ከ 2 መቶ 30 ሺ በላይ ነዋሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።

መቶ 61 ሺ 7 መቶ ቀሪ ተመዝጋቢዎች በመኖራቸው ባለፉት ወራት በተሰሩት ስራዎች 30 ሺ ነዋሪዎችን መመዝገብ መቻሉን ም/ከንቲባ ሀርቢ ገልፀው፤

በአጠቃላይ ከመቶ 31 ሺ እስከ መቶ 33 ሺ የሚሆኑ ቀሪ ነዋሪዎች በመኖራቸው ሙሉ በሙሉ ነዋሪዎችን የመታወቂያው ባለቤት እንዲሆኑና የታቀደውን ዕቅድ በአጭር ጊዜ ውስጥ በውጤታማነት ለማጠናቀቅ ስራዎችን በመከፋፈል

ከወረዳዎችና ከሴክተር ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በመጨረሻም ም/ከንቲባ ሀርቢ ነዋሪዎች የብሔራዊ ዲጅታል የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት የመስራቱ ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው፤የፋይዳ መታወቂያ እንደስሙ ፋይዳው የላቀ በመሆኑ ምዝገባውን ያላከናወኑ የድሬዳዋ ነዋሪዎች በየአካባቢው በተዘጋጁ ኪቶች ምዝገባ በማከናወን የመታወቂያው ባለቤት እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በኤደን ሳሙኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *