የወጣቶች ወርቃማ ጊዜያት ላይ ትኩረቱን ያደረገ አዲስ የነሺዳ ስብስቦችን የያዘ የወጣት ሙአዝ መሀመድ አልበም በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን በገኙበት በዛሬው እለት በድምቀት ተመርቋል።
በምረቃ መርሀግብሩም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ክብር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተገኝተው እንደገለጹት ወጣቱ በነሺዳ አልበሙ በተለይም በለጋ እድሜው ለሀገር ለቤተሰብ የሚጠቅም ተግባራትን በጥበበ በማዋዛት ላበረከተው አስተዋጾ ምስጋና አቅርበዋል።
ወጣቱ በርካታ ውጣውረዶችን በማለፍ ለዚህም ግብ በመድረሱም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በቀጣይም ወጣቱ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ለሚያደርጋቸው በጎ ተግባራት ላይ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክብር አቶ ሀርቢ ቡህም በበኩላቸዉ በአስተዳደሩ የኪነጥበብ ዘርፍ ልማት እየተነቃነቀ የመጣበት መሆኑን አንስተው በዛሬውም እለት በርካታ ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚያነሳው ሽባብ የተሰኝው አልበም ምርቃትም ለዘርፎ እድገት ከፍተኛ አስተዎጾ እንዳለው ተናግረዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብር አቶ ኢብራሂም ይሱፍም ወጣቱ ማሀህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በበጎ ተግባራት በመሠማራት ምሳሌ መሆን የቻለ እና ወጣቶች ለሀገራቸው ማበርከት ስለሚገባቸው ተግባራት በጥበብ ነቅሶ በማውጣት ጥሩ የአልበም ስራ መሠራቱን ገልጸዋል።
“ሸባብ” የሚል መጠሪያ ያለው የነሺዳ አልበም ወርቃማ የወጣትነት ወቅትን በአግባቡ በመጠቀም ለቤተሰብ ለሀገር የሚጠቅም ተግባራትን መፈጸም እንደሚገባ የሚያስተላልፍ የነሺዳ አልበም መሆኑን ወጣት ሙአዝ መሀመድ ገልጿል።
የነሺዳው ስብስቦች ወጣቱ በተስፉ መቁረጥ ከአስከፊ የስደት ሂወት በመግባት ወደ ግብ እንዳይደርሱ ከሚያደርጋቸው ተግባራት ወጥቶ በማበረታት ጊዜውን ፍሬያማ ማድረግ ላይ ያተኮሩ መሆናቸው እና ታላቁ የረመዳን ወር ጾም መግባቱን ተከትሎም የተካተቱ ስራዎች መኖራቸውንም ገልጿል።
በምረቃ መርሃ ግብሩም የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ሱልጣኖች እና የኪነጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተዋል።


