የሆር ሙድ ጤና ቡድን 1447ኛው የረመዳን ፆም አስመልክቶ የተለያዩ የፍጆታ እቃዎች ድጋፍ አበርክቷል።በመረሀ ግብሩ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተጋባዥነት ተገኝተዋል።
በድጋፉ መረሀ ግብሩ ተጋብዘው የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር እንደተናገሩት በአገር አቀፍ ደረጃ የማእድ ማጋራት የበጎ ፍቃድ ስራዎች በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተነሳሽነት መከናወን ከጀመረ ወዲህ በርካታ ተግባራት እየተፈፀሙ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ወትሮውንም ድሬዳዋ አስተዳደር በመደጋገፍና በመተጋገዝ እሴት የዳበረ እንደነበር ገልፀው በተለይም በፆም ወቅቶች ወቅት መደጋገፍና መረዳዳት ጎልቶ እንደሚታይ አብራርተዋል።
የሆርሙድ የጤና ቡድን ዛሬ ያበረከተው የማዕድ ማጋራት ድጋፍ በመሰል መሀበራት መደገምና መጠናከር ይገባዋል ሲሉ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል የብልፅግና ፓርቲ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ /ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ በአገራችን ከለውጡ ወዲህ ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር የሆኑ ፖሊሲና ስትራቴ ጂዎች ተቀርፀ ተግባር ላይ እየዋሉ መሆኑን ገልፀዋል።
ስፖር ወዳጅነትን ፍቅርን ማጠናከሪያ መድረክ ነው ያሉት አቶ ኢብራሂም ከስፖርት ባለፈ የሆርሙድ ጤና ቡድን እንዳከናወነው ሁላችን ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት መበርታት ይገባናል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የድሬዳዋ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ካሊድ መሀመድ የበጎ ፈቃድ ስራዎች እንደ አስተዳደር በተቀናጀ ምልኩ ለመተግበር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ባለፉት ጊዜያት በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎች 82ሺ የአስተዳደሩን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ይህ የበጎ ፈቃድ ስራ በይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።ወጣቶች ባሉበት ሁሉ የበጎ ፈቃድ ስራና ማከናወን እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
ሳሚ ጀማል የሆርሙድ ጤና ቡድን ም/ፕሬዝዳንት ዛሬ በጤና ቡድኑ አባላት ሙሉ ተሳትፎ መዋጮ የረመዳን ፆምን አስመልክቱ የተደረገው ድጋፍ 6መቶ ሺ ብር የሚያወጣ እንደሆነ 50 ሰዎችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርገ ተናግረዋል።
በቀጣይም የጤና ቡድኑ ይንን ተግባር በተለያዩ መልኩ እንደሚያስቀጥል አስረድተዋል


