“ድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠና እና የምስራቁ የሀገራችን ኢንዱስትሪ መዕከል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የእድገት ግስጋሴዋን የሚመጥን የውሃና ሳንቴሽን አገልግሎት በእጅጉ ያስፈልጋታል”:- የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር
በድሬዳዋ አስተዳደር ከአንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን( 1. 3 ቢሊዮን) ብር በላይ በሆነ ወጭ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ ማጣሪያና ማስወገጃ የኦፕሬሽንና ጥገና ፕሮጀክት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል። በዚህም በመርሃ-ግብሩ የተገኙት ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የግንባታ ፕሮጀክቱ የአስተዳደሩን የፍሳሽ አያያዝና አወጋገድ ስርዓትን በላቀ ደረጃ የሚያሻሽል መሆኑን ተናግረው፤ ድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠና እና የምስራቁ የሀገራችን ኢንዱስትሪ መዓከል ከመሆኗ ጋር…


