ድሬን ፅዱ፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማት ስራዎች በጥራትና በፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በከተማችን እስካሁን በኮሪደር ልማት ስራ የተጠናቀቁ የመንገድ እና ሌሎች መሰረተ ልማት ስራዎችን ስንመለከት:-
• 21 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ግንባታ
• 18 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ ግንባታ
• 22 ኪ.ሜ የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማት ስራ
• 6.20 ኪ.ሜ የመንገድ አካፋይ ማስፋት እና ግንባታ ስራዎች
• 276 የመንገድ ዳር መብራት (Smart Pole) ስራ እንዲሁም ከ 406 በላይ የመንገድ ዳር ቋሚ ስትሪፕ መብራቶች እና 124 ፍሬ ሶላር መብራቶች ተከላ ስራ
• 6 የአውቶቢስ ፌርማታ ሼድ (ጥላ) ስራ
• 28 ኪ.ሜ የጎርፍ ፍሳሽ ማስዎገጃ ስራዎች ተከናውነዋል።
በተቀናጀ መልኩ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ስንመለከት ደግሞ ማለትም የቴሌ-ኮሚኒኬሽን፣ የውኃ እና የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ስራዎች 21.96ኪ.ሜ የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ 20.28ኪ.ሜ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 14.11ኪ.ሜ የቴሌኮም መስመር ዝርጋታ ስራዎች ተከናውነዋል።
የምድረ ገጽ ማስዋብ፣ ፋውንቴን፣ ስፖርት ማዘውተሪያ እና የህጻናት መዝናኛ ስፍራዎችን በተመለከተም አራት ፋውንቴን (የምድረገጽ ያለው) እንዲሁም ሁለት የምድረገጽ የማስዋብ ስራዎች፣ አንድ የህጻናት መዝናኛ ስፍራ፣78 አግዳሚ እና 230 የአበባ ቅርጽ የመንገድ ዳር ማረፊያ ወንበሮች፣ የመኪና ቻርጂንግ ስቴሽን፣ ፓርኪንግ ቦታዎች፣ ካፌ፣ ሱቆች እና የህዝብ መዝናኛዎች ተገንብተዋል።
በተጨማሪም ቻርጂንግ ስቴሽን (ማዕከል) ጋር በተያያዘ 24 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል 12 ፈጣን ባ ለሁለት ገን ቻርጀር፣ 5 የመኪና ፓርኪንግ ስቴሽኖች/ቦታዎች፣ 5 የህዝብ መዝናኛ ካፍቴሪያዎች፣ 40 ሱቆችና 5 የህዝብ ሽንት ቤቶች ( 3 አዲስ፣ 2 የታደሰ) በተጨማሪም አምስት አረንጓዴ ቦታዎች (ላንድ እስኬፕ) (አንድ ፋውንቴን የሌለው) ተሰርቷል።
ከላይ በዝርዝር ከተመለከትነው በተጨማሪም ሌሎች ተያያዥ የኮሪደር ልማት ስራዎች 215 ሜትር የፍርድ ቤቶች አጥር ስራ፣1,131 ሜትር የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ፓርክ አጥር ስራና የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የበር፣ አጥር፣ ፓርኪንግ እና አረንጓዴ ልማት ስራ ተከናውነዋል።
በአጠቃላይ በድሬዳዋ ኮሪደር ልማት ስራ 12 ኪ.ሜ የተከናውኗል፤ ከ 2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ልማቱ የሸፍነው በጀት ሲሆን ከዚህ ውስጥ ታዲያ 8% የሚሆነው ከቬራ ፓስታ እስከ አኳ ኡኖ (2.8 ኪ/ሜ) እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የተሸፈነ ነው።


