ልዑኩ ለ2027ቱ 36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለማከናወን ነው ድሬዳዋ ከተማ የገባው።
ልዑኩ ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የድሬዳዋ ወጣቶችና ሰፖርት ኮሚሽን ሰፖርትን የማልማት እና ማሰፊፊት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ኢብሳ ዱሪ፣ የድሬደዋ ሰፖርት ምክር ቤት አባል አቶ አሕመድ አብዶ እና በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ከጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድሬዳዋ የገባ ሲሆን፤ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በመጪው ማክሰኞ በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።


