“ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጭነት ምዝገባ በማከናወናን የሚበጀንን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል”:- የድሬዳዋ ነዋሪዎች

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጭነት ካርድ በማውጣት የሚበጀንን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ምርጫው የሀገርን መጻዒ ዕጣ ፈንታ የሚወስን ዜጎች ሕገ-መንግስታዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የሚጠቀሙበት ጊዜ በመሆኑ ማኛውም ዕድሜው ለምርጫ የደረሰ ዜጋ ሁሉ ይህንን መብቱን በአግባቡ ሊጠቀምበት እንደሚገባም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡

‎ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን ለመጠቀም የመራጭነት ምዝገባ ጊዜው ሳይጠናቀቅ ከወዲሁ የመራጭነት ካርድ እንዲወስዱም ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አማካይነት የቀረበው “ምርጫዬ” የተሰኘው የምርጫ መመዝገቢያ ቴክኖሎጂ በቀላሉ የምርጫ ምዝገባ ለማካሄድ እንደረዳቸውም አስተያየት ሰጪዎቹ አያይዘው የተናገሩ ሲሆን መተግበሪያው የመራጮችን ጊዜ የቆጠበ እና ምቹ ሁኔታንም የፈጠረ መሆኑን አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *