“ያልዘሩት አይበቅል፣ ያልለፉበት አይቆረስ” እንዲሉ ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት በላቧ የገነባችው የሪፎርም መሠረት ዛሬ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል።
የቀድሞውን የተለመደ የኢኮኖሚ መንገድ በመቀየር፣ በሀገር በቀል ዕውቀት እና በብዝኃ ዘርፍ የታገዘ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ተከፍቷል።
ግብርናን ብቻ ሙጥኝ ማለትን ትተን፣ በአምስቱ የኢኮኖሚ ዓምዶች (ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ቴክኖሎጂ) ላይ የተገነባው መዋቅር ሀገራዊ ምርታማነታችንን አሳድጎታል።
በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ የታየው ተዓምር የውጭ ጥገኝነትን ሰብሮ ኢትዮጵያን ወደ ውጭ ላኪነት አሸጋግሯታል።
በሌማት ትሩፋት አማካኝነትም የምግብ ሉዓላዊነታችን በየቤታችን ጓሮ መረጋገጥ ጀምሯል።
ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች የተደረገው ሽግግር እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የሕክምና እና የግንባታ ግብዓቶች ኢንዱስትሪውን አነቃቅተዋል።
ይህ ሁሉ ስኬት በአረንጓዴ ዐሻራ ታጅቦ፣ የሀገራችንን የደን ሽፋን ወደ 23.6 በመቶ ከፍ በማድረግ ለትውልድ የሚተርፍ አረንጓዴ ቅርስ አኑሯል።
ዛሬ የምናየው የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት እና የኤክስፖርት ዕድገት የነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ አብሳሪዎች ናቸው።
የዛሬው ላባችን የነገው የድል አክሊላችን ነውና፣ የተጀመረው የልማት ጉዞ በላቀ መነሣሣት ይቀጥላል!


