በሆቴል አገልግሎት የሚሰጡ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፤ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ተጎብኝቷል።
በግንባታው ሂደት ላይ ያሉ እነዚህ ሆቴሎች ሲጠናቀቁ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር እና የአስተዳደሩን ኢኮኖሚያዊ ገቢ በማነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብሎ ይታመናል።
በመስክ ምልከታው የተቃኙት ሆቴሎች ከባለ አራት እስከ ባለ ስምንት ወለል ህንፃዎች ሲሆኑ ፣ ዘመናዊ የመኝታ ክፍሎችን ጨምሮ ደረጃቸውን የጠበቁ የመሰብሰቢያ አዳራሾችንና የተለያዩ አገልግሎቶችን የያዙ ናቸው።
በቀጣይም ሌሎች መሰል በዘርፉ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ጉብኝት እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።


