ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው የከተማዋን የኮሪደር ልማትና የከተማ እድሳት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ሁሉን አቀፍ ፕሮጀክት፤ የኦሎምፒክ ደረጃን ያሟላ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ እና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎችን እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን፣ ዘመናዊ የቤት እና የዉጪ ጂም ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ከማህበረሰብ አገልግሎቶች ጋር አቀናጅቶ የያዘ ነው። ልማቱ ሁሉንም የእድሜ ክልሎች ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፣…


