በክላስተሩ 9 ቀበሌዎች /አዲጋ ፈለማ፣ ሁላ ሁሉል ፣አሰሊሶ ፣ጋደንሰር ፣ጎላ አደግ ፣ ቦረን ፣ ገንደ ሪሄ ፣ለገ ሀሬ ፣ ለገ ዶል/ ፓርቲውን የሚወክሉ እጩዎችን ባሰተዋወቁበት መድረክ የድሬደዋ አስተዳደር ምክርቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ከሪማ አሊ በዘንድሮው ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ በአስተዳደራችን የተሻለ እውቀት፣የትምህርት ዝግጅት እና የአመራር ብቃት ያላቸውን እጩዎችን ፆታን ባማከለ መልኩ ስነ-ምግባር እና አፈፃፀማቸው በፓርቲው ታይቶ ለእጩነት መቅረባቸውን ተናግረዋል።
ባለፉት ስምንት ዓመታት በአስተዳደሩ የመጣውን የእንድነት እና አብሮነት እሴትን በመጪዎቹ አምስት ዓመትን ለማስቀጠል የህዝቡ ድምፅ ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን ድሬዳዋን ጉልበት ፣ አውቀት እና ልምዳችንን በማፍሰስ ወደ ተሻለ ብልፅግና ለማሸጋገር ፓርቲው እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከህዝቡ ጋር እንደሚሰራ ገልፀዋል።


