በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በዛሬው እለት ድሬዳዋ ገብተዋል
ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀሙድ ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አብዲ ሙክታር ፣ ኡጋዞች የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸል።


