ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት በላቀ ውጤት መቀጠሉን ገለጹ
የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት በላቀ ውጤት መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱልልታ ወረዳ በመገኘት፣ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ማሳን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።


