የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ሰኞ የሚካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ገለጹ::
የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 የሚካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል። አስተያየታቸውን ለኢቢሲ የሰጡ ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ መራጩ ሕዝብ ለሀገር ሰላም፣ አንድነትና ዕድገት ያግዛል ያለውን ለመምረጥ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል። ከተሳታፊዎቹ መካከል ወጣት ዳግማዊት አዲሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የመምረጥ ዕድል በማግኘቷ ቀኑን በጉጉት እየጠበቀችው መሆኗን ገልጻ፣ ለመምረጥ መዘጋጀቷን ተናግራለች። በተመሳሳይ መልኩ፣ ሙፈርያት ታዬ ለመምረጥ…


