ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ትምህርት እየተሰጠ ነው

ነገ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት ይረዳ ዘንድ ስልጠና ወስደው የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች በመላው ሀገራችን የመራጮች ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ።

በድሬዳዋ ከተማም በገጠር ክላስተሮችና በከተማዋ ውስጥ በጎ ፈቃደኞች በመንቀሳቀስ ይህንን ትምህርት እየሰጡ መሆናቸው ታውቋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎችም እየተሰጠ ያለው ትምህርት በቂ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልጸው፣ ይህም በምርጫው ዕለት ያለምንም ስህተት አስፈላጊውን ድምፅ ለመስጠት እንደሚረዳቸው አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *