በነገው ዕለት በሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን የድሬዳዋ ነዋሪዎች ገለጹ::
በነገው ዕለት በመላ ሀገሪቱ የሚከናወነውን ሰባተኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ያነጋገራቸው የወረዳ አንድ ነዋሪዎች ገለጹ። የምርጫ ካርድ የበይነ-መረብ (ኦንላይን) መተግበሪያ ተጠቅመው መውሰዳቸውን የሚናገሩት የወረዳ 01 ነዋሪው አቶ ረመዳን ሰይድ፤ ለነገው ዕለት ከየትኛውም ጉዳይ በላይ ቅድሚያ በመስጠት፣ በአምስት ዓመት አንድ ጊዜ የሚገኘውን የመምረጥ ዕድል በጠዋት ለመጠቀም መወሰናቸውን…


