ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንዱን እና ትልቁን ዲሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቷን አጠናቃ ዜጎች ይበጀኛል ያሉትን ድምፅ ለመስጠት ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል።
7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ነገ ግንቦት 24/2018 ዓ/ም ይካሄዳል ምርጫውን ለማካሄድም በአስተዳደሩ በወረዳ 02 የሚገኙ ነዋሪዎች የሀገሪቱ ሰላምና ልማት ያስቀጥላል የምንለውን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ስሉ ገልፀዋል።
ህብረተሰብም ነገ ለሚደረገው ምርጫ በነቂስ ወጥቶ በካርድ የሚበጀውን ድምፅ በመሰጠት የነገውን መጺዓ እድል መወሰን ይጠበቅበታል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በወረዳው ተዘዋውረን እንደተመለከትነውም በሁሉም የድምጽ መስጫ ጣቢያ ነገ ለሚካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የተለያዩ የቁሳቁስ ግብዓት ዝግጅት እየተካሄደ ሲሆን ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም የጸጥታ አካላት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተመልክቷል ።


