የወረዳ 04 አስተዳደር ነዋሪዎችም በነገው እለት በሚካሄደው 7 ተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫም ለሀገራችን እንዲሁም ደግሞ ለአስተዳደራችን በቀጣይ አመታት የተሻለ ስራዎችን ይሰራል ብለን ያመኑበትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
7 ተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫም ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚወጡ ነው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ያስታወቁት ።በነገው እለትም ከማለዳው 12 ሰዓት አንስቶ ነዋሪው ህብረተሰብ በሚቀርባቸው የምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ እንዲመርጡም ጥሪያቸውን አቅርበዋል ::


