በድሬደዋ አስተዳደር ወረዳ 8 የምርጫ ዝግጅት ምን ይመስላል….!!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀጣዩን የእድገት፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ምዕራፍ የምታረጋግጥበት ታሪካዊው ሀገራዊ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እየተቃረበ ይገኛል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ደግሞ የቅድመ ምርጫ ዝግጅቶች ወሳኝ ሚና አላቸው።

​በአሁኑ ወቅት በድሬደዋ አስተዳደር የምርጫ አስፈጻሚ አካላት፣ የጸጥታ መዋቅሩ እንዲሁም መላው ማህበረሰብ ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ ኩነት በአንድነት እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

በአስተዳደሩ ወረዳ 8 ነዋሪ ወጣት አብዱልጀባር አህመድ በዚህ ታሪካዊ ሁነት ላይ ሲሳተፍ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለፅ የመምረጥ መብቴን በመጠቀም ይሆነኛል ይበጀኛል ለሀገር እድገት እና ቀጣይነት ላለው እድገት ይጠቅማል ብየ የማስበውን ተመራጭ ለመምረጥ በጉጉት እየጠበኩ ነው ሲል ገልጿል ።

ወ/ሮ ማህደር ምርጫ ለአንድ ሀገር የሰላም እና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባት ያለውን ወሳኝነት በማንሳት በዚህ ታሪካዊ ሁነት የራሷን አሻራ ለማሳረፍ በመጠባበቅ ላይ መሆናኗን ተናግራለች ።

ዲሞክራሲን መገንባት በአንድ ጀምበር የሚጠናቀቅ ሳይሆን፣ በእያንዳንዱ ዜጋ ንቁ ተሳትፎና በሂደት የሚጎለብት የጋራ እሴት ነው። ይህንን እሴት በተግባር የምናሳይበት ሌላው ታሪካዊ ምዕራፍ እንደሆነም ገልፃለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *