direcom

ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም እና ብልጽግና ዋስትና የሚሆን ዘመናዊ ሠራዊት ገንብታለች – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በልዩ ዘመቻዎች 65ኛ ዓመት በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ ራዕይ ለትውልድ የሚሸጋገር ስትራቴጂያዊ ተቋም መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የልማት እሳቤ ውኃን እንደ ልማት እና ሕይወት ምንጭ ማየት መጀመሩን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ አስተሳሰብ በወታደራዊው ዘርፍም ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣቱን አስረድተዋል። ቀደም ሲል በየብስ እና በተራራ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ “የሐዋሳን ብርሃን፣ የሕዝቡን ፍቅር እና ታሪካዊ ማንነቱን በቅዳሜ እና እሑድ እየመጣችሁ እንድትጋሩ፣ የእኛን ደስታ ተካፈሉ” ሲሉ ከሐዋሳ ግብዣ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ65ኛው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የምሥረታ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ስለ ሐዋሳ ሲገልጹ፣ “ሐዋሳ የኢትዮጵያ ሁነኛ ራዕዮች የሚበሠሩበት፣ ቄጤላ በውስጥ የሸሸግነውን፣ በቤት የመከርነውን፣ በዝማሬ የምንገልጽበት፣ ይህ ቦታ በተደጋጋሚ ያለምነውን የተናገርንበትን ስናሳካም በጋራ ድል ያበሰርንበት ቦታ ስለሆነ፤ ለመላው የሲዳማ ሕዝብ በተለይም ቄጤላን በውብ መንገድ ላቆዩልን አባቶች የከበረ ምስጋናዬን ላቀርብ እፈልጋለሁ” ብለዋል። የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ…

Read More

የሰው ልጅ ጥረትና ብርታት ማንኛውንም በረሃ ወደ ገነትነት የመቀየር አቅም እንዳለው የብላቴ አካባቢ ለውጥ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብላቴ አካባቢ ልማትን በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት፣ ከሦስት ዓመት በፊት በረሃ የነበረው ስፍራ ዛሬ በዘመናዊ መስኖ ለምቶ የሙዝ፣ የአቮካዶ እና የሃብሃብ ምርቶች የሚገኙበት ጥቅጥቅ ያለ “ጫካ” መምሰሉ እጅግ የሚያስደንቅ ነው። በሲዳማ ክልል በ”ሌማት ትሩፋት” የተመዘገበው ውጤትም የዚሁ ስኬት አካል መሆኑን ጠቅሰው፣ የዶሮ ምርት ከጥቂት ሚሊዮኖች ተነስቶ ወደ 15 ሚሊዮን ማደጉ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገው…

Read More

ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም የብልፅግና ጉዞዋን ለማፋጠን ቀን ከሌት እየተጋ ያለ ፓርቲ መሆኑ ተገለፀ

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 05፣ 06፣ 08 እና 09 የብልፅግና ፓርቲ የ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ብልፅግና ፓርቲ ሀገራችን ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም የብልፅግና ጉዞዋን ለማፋጠን ቀን ከሌት እየተጋ ያለ ፓርቲ መሆኑ ተገልጿል። በመርሃ-ግብሩ ሲሳተፉ ያነጋገርናቸው የብልፅግና ፓርቲ አባላት “የስንዴ ነዶ” የመደመር፣…

Read More

ታሪክ ከማይዘነጋው የመለዮ ለባሽ የአዲስ ምሩቃን፣ በተለይም በርከት ያሉ ሴት አየር ወለዶች የተመረቁበትን በዓል በጋራ በሀዋሳ ከተማ ለማክበር በመገናኘታችን የተሰማኝን ታላቅ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።

“የእኛ ተልዕኮ ራዕይ ያለው ለትውልድ የሚሻገር ሁነኛ ተቋም መፍጠር ነው። የእኛ ተልዕኮ ውጊያ የሚያስቀር፣ ውጊያ የሚጨርስ Elite Force መገንባት ነው። የእናንተ ተልዕኮ ኢትዮጵያን መገንባት፣ ኢትዮጵያን መጠበቅ፣ ኢትዮጵያን ማጽናት እና ኢትዮጵያን ማሸጋገር ነው።” ኢትዮጵያ በልጆቿ ላብ ትሰራለች፣ ኢትዮጵያ በልጆቿ አጥንት እና ደም ትጸናለች፤ ኢትዮጵያ አልተደፈረችም አትደፈርም፤ በክብር እና በነጻነት ለልጆቻችን የምናሸጋግራት ብቸኛዋ የአፍሪካ ፈርጥ ሆና ትቀጥላለች።…

Read More

“የኢትዮጵያ ሠራዊት የንድፈ ሐሳብ ሳይሆን የተግባር ኃይል መሆኑን በተግባር አሳይቷል” – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በ65ኛው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የምሥረታ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከውስጥ እና ከውጭ የተሰነዘሩባትን ዘመነኛ ጥቃቶች በብቃት መክታ ወደ ላቀ ከፍታ መሸጋገሯን ገልጸዋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “እኛ ኢትዮጵያውያን የትልቅ ሕዝብ እና ሀገር ባለቤት ነን” በሚል ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት መላው ሠራዊት…

Read More

የ44ኛ ዙር ንጋት ኮርስ የኮማንዶ ሰልጣኞች ተመረቁ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት እያከበረ ይገኛል። ዕዙ በዚህ በዓሉ ላይ የ44ኛ ዙር ንጋት ኮርስ የኮማንዶ ሰልጣኞችን አስመርቋል። በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ለተመራቂዎቹ የቀይ መለዮ የመልበስ ፈቃድ የሰጡ ሲሆን፣ በስልጠናቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎችም መለዮ አልብሰዋል። የዕዙ…

Read More

ለሕዝባችን መከታ፤ ለኢትዮጵያ ጠላቶች ደግሞ መቅሰፍት ነን – ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለመንግሥት መከታ፣ ለጠላቶቿ ደግሞ መቅሰፍት ነው ሲሉ የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገለጹ። በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የዕዙ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና አዛዡ፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች ከጥፋት ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ የሠራዊቱ ክንድ ብርቱ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። ጀግንነት የኢትዮጵያ ቀደምት የታሪክ አሻራ መሆኑን የጠቀሱት ሌተናል ጄኔራል…

Read More

የኮሪደር ልማት ስራዎች በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

‎‎የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገርን ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ በሐዋሳ ከተማ በሁለተኛው ምዕራፍ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በዛሬው ዕለት ተመልክተናል ብለዋል። የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገርን ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤…

Read More

የልዩ ዘመቻዎች እዝ በየትኛውም ጊዜና በማንኛውም ሁኔታ ግዳጁን በብቃት ለመፈጸም በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በታላቅ ወታደራዊ ትዕይንት እያከበረ ነው። ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ሀገር ያጸኑ የበርካታ ጀግኖች ምድር ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝም ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ የማይበገር ጽናት ይዞ ኢትዮጵያን ያኮራ ጀብዱ ፈጽሟል ብለዋል። እዙ አሁን ላይ በመከላከያ ሪፎርም ስራዎች…

Read More