በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ማህበር የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ ።
በምስጋና ዝግጅቱ ላይ ከንቲባ አህመድ ቡህ እና አቶ እዝቅያስ ታፈሰን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸውና በቀድሞው ጊዜ ስመጥር የነበሩ መቶ የሚሆኑ ስፖርተኞችና መምህራን ተገኝተዋል። የኮረና ወረርሺኝ መከሰቱን ተከትሎ የቀድሞ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች በነበረው አቶ ተካበ ዘውዴ አነሳሽነት እርስበርስ መደጋገፍን መነሻ ያደረገው በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ማህበር በድሬዳዋ ለሚገኙ የአረጋውያን ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገ…


