ህብረተሰቡ የሞተር አልባ ትራንስፖርትን በማዘውተር የተሸከርካሪ መጨናነቅ በማስቀረት የትራፊክ አደጋን ሊቀንስ እንደሚገባ በፌደራል ትራንስፖርት የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ሁለተኛውን ዙር የሞተር አልባ ትራንስፖርት ቀን የፊታችን እሁድ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች በድማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት በተለይም የሞተር አልባ ትራንስፖርትን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ለማበረታታት፤የብስክሌት ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለማሳደግና አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ለማጎልበት ፤እግረኞችን ለማበረታታት ነው ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። በዚህም በ2012 ዓ.ም የጸደቀውን የሞተር አልባ ትራንስፖርት…


