በአከባቢ ልማት ዙሪያ የአስተዳደሩ አመራሮች ዉይይት አካሄዱ ::

    የድሬደዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና የ 9ኙ የከተማ ቀበሌ ስራ አስፈፃሚዎች የተሳተፉበት በአከባቢ ልማት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረና ባለፉት አመታት የተከናወኑ የአከባቢ ልማት ስራዎች ዙሪያ ዉይይት ተካሄደ ፡፡ በዚህ የዉይይት ላይ የመክፈቺያ ንግግር ያደረጉት የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ጀማል በልማት ስራዎች ህብረተሰቡን አሳታፊ ማድረግ የልማት ስራዎቹን ህዝቡ በባለቤነት እየተከታተለ እንዲሰሩ ከማድረጉም በላይ ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡም…

    Read More

      Kulan uu soo diyaariyay xafiiska dhismaha iyo horumarinta magaalada oo lagaga wada xaajoonaayay sidi kor loogu qaadi lahaa mashaaricaha horumarineed ayaa ka qabsoomay holka shirarka e eras huteel.

      Kulankani oo ay kazoo qayb galeen masuuliyinta sarsare ee ismaamulka iyo gudoomiyayaasha 9ka qabale ee magaalada ayaa waxaa furitaanki kuankani ka hadlay mudane injineer Jamaal ibraahim oo ah madaxa xafiiska dhismaha iyo horumarinta magaalada ayaa sheegay in mashaaricaha oo laga qayb galiyo bulshada ay abuuri karto cad caadaan iyo waliba in ay mashaaricdasi yeeshaan tayo…

      Read More

        “መምህራን በቀውስ ጊዜ ይመራሉ፤ መጪውንም ይተነብያሉ!” በሚል መሪ ቃል የመምህራን ቀን በአስተዳደራችን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

        የመማር ማስተማር ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ የመምህራን የሙያ ብቃትና በተለይም ብቁ ዜጋ ከማፍራት ጎን ለጎን የሀገራችን የብልፅግና ጉዞ መምህራን የላቀ ሚና መጫወት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ አንደገለፁት ዛሬ በዓለም ላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ ሀገሮች ለስኬታቸው ዋናው ምክንያት ለትምህርት ትኩረት በመስጠታቸው ሲሆን በዚህ ረገድ መምህራን ሙያቸውን…

        Read More

          ህብረተሰቡ ሰላሙን በማስጠበቅ እርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህሉን እንዲያጠናክር ጥሪ ቀረበ።

          የድሬደዋ አስተዳደር በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ወይይት አድርገዋል። በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሀር ድሬዳዋ ያሳለፍናቸው ወራት በህብረተሰቡና በፀጥታ አካላት ትብብር ብዙ ዋጋ በተከፈለበት መስዋዓትነት ወደ ቀድሞ ሰላሟ መመለሷን በመጠቆም ይህንን ሰላም ሊያደፈርሱ የሚፈልጉ ቀን ከሌት የማይተኙ በሰው ህይወት ቁማር የሚጫወቱ አረመኔ…

          Read More

            የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን በመከላከል የ2013 የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማስጀመር ውይይት አካሄደ፡፡

            በዩኒቨርሲቲው ውስጥም ተማሪዎችን በዘር፣ በሀይማኖትና በብሔር የሚከፋፍሉ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራኞች ላይ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ እንደማይታገስ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢና የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ተቋማት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር አለሙ ስሜ ገልፀዋል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ 2013 የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር ይረዳ ዘንድ የተለያዩ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎችን በማከናዎን ላይ የሚገኝ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ያሉትን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችንም ከዚህ ቀደም የዩኒቨርሲቲው የቦርድ…

            Read More

              በድሬደዋ አስተዳደር ስር በሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች በፍጥነት ተፈትሸው ሊታረሙ እንደሚገባ ተገልጋዮች ገለፁ፡፡

              የአስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተመረጡ አራት የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ከሚዲያ ጋር በመቀናጀት ድንገታዊ ምልከታ አድርጓል፡፡ በአስተዳደሩ ከፍተኛ ተገልጋይን ከሚያስተናግዱና የህዝብ ሮሮ በስፋት ከሚነሳባቸው ተቋማት መካከል በሁለት የቀበሌና በሁለት መንግስታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የአስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ሚዲያዎች ጋር…

              Read More

                ከድሬዳዋ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ::

                የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ በህወሃት አገር አጥፊ ቡድን ላይ በሚወሰደው እርምጃ ከፌዴራል መንግስት ጎን ይቆማል ። የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ ሀገርን ከመበተንና የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ በህወሃት አጥፊ ቡድን ላይ የመከላከያ ሰራዊታችን በሚወስዳቸው ማንኛውም አይነት እርምጃዎች የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ይገልፃል ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ ህወሃት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ያደረሰውን ጥቃት በእጅጉ ያወግዛል ፡፡ በሀገራችን…

                Read More

                  የኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ::

                  የኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ጥቅምት 25/2013 ባደረገው 21ኛ አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ መንግሥት የሀገርን ሰላምና ሕልውና፣ የሕዝብንና የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ እና ሀገሪቷን ወደ ሁከትና ብጥብጥ የሚወስዱ ማናቸውንም ድርጊቶችን የመከላከል ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን በመገንዘብ፤ እንዲሁም በትግራይ ብሔራዊ ክልል ውስጥ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን እንዲሁም የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ አደጋ ላይ የሚጥሉ በተለይም የሀገርን ሉዐላዊነት…

                  Read More

                    Golaha wakiilada ismaamulka diri dhabe ayaa ee sanad hawleedkoodi 2aad kalfadhigisi caadiga ahaa 45aad yeelan doona 26 iyo 27 bisha diqimti.

                    Afhayeenka golaha baarlamaanka ee ismaamulkani diri dhabe marwo faduum mustafe ayaa shir jaraa`id oo ay la yeelatay warbaahinta sheegtay in kalfadhigani lagu qiiman doono waxqabadki rubici koobaad ee sannad miisaniyeedkani 2013 TI ee xafiisyada caafimaadka iyo waliba laydhi tiriiga ama kooraanka sidoo kale waxay marwo faduun sheegtay in la buuxin doono gudiyada joogtada ah ee…

                    Read More

                      የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የምክር ቤቱን 2ኛ የስራ ዘመን 45ኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል::

                      ክብርት አፈ-ጉባኤዋ በመግለጫቸውም ጥቅምት 22/2013ዓ.ም በምእራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወገዙ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ የስራ ዘመን 45ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከጥቅምት 26 እስከ 27 ድረስ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚያካሂድና በጉባኤውም የምክር ቤቱን የ44ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ ‘የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ…

                      Read More