በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ የሚመክር ውይይት አካሄደዋል፡፡

    በድሬዳዋ የትግራይ ተወላጅ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ባካሄዱት ውይይት በቅርቡ የትግራይ ክልል በሚያስተዳድረው ህወሓት በመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የፈፀመው ኢ-ሠብአዊ ድርጊት ፍፁም የትግራይ ህዝብን የማይወክል መሆኑን ያወገዙ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ከኢፌድሪ መንግስትና ህዝብ ጎን መሆኑንም በተግባር እንዳረጋገጠው ሁሉ አሁን ከአዲሱ የትግራይ አስተዳደር ጎን በመቆም ለዘላቂ ሠላምና ልማት በጋራ እንደሚሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
    በድሬደዋ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችም በሚፈለጉ ነገሮች ሁሉ ከኢፌድሪ መንግስትና ህዝብ ጎን መሆናቸውን ገልፀዋል ።
    ‹‹ጠንካራ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና›› !!!
    በውይይቱ ላይ የተነሱ ነጥቦች መካከል መንገዱን የሳተው የህወሃት ትግል አቅጣጫ፣ የትግራይ ህዝብና የህወሃት ቡድን ልዩነት፣ የጁንታው ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት እና አዲሱ ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፊቱ ያሉትን ሥራዎች በስፋት ተወያይተዋል፡፡
    በመጨረሻም በውይይቱ ህግ ማስከበር ዘመቻ የትግራይ ህዝብ የሚጠቅምና ከጁንታው አፋኝ ነጻ የሚያወጣ ስለሆነ አሁንም የትግራይ ህዝብ ይህንኑ ጁንታ ቡድን ለህግ እንዲቀርብ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡