የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና የድሬደዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የጋራ መግባቢያ ተፈራረሙ::

    የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና የድሬደዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ የተፈራረሙት የጋራ መግባቢያ ተቋማት እንደ ድሬ ደዋ እና በሀገራቀፍ የተሰጣቸዉን ተለዕኮ በተሻለ ዉጤት ለማሳካት ለጋራ የተቋማት ተቀናጅተዉ መስራት ወሳኝ በመሆኑን በመግባቢያ ስነ-ስርዓት ፊርማዉ ላይ የመክፈቺያ ንግግር ያደረጉት መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ገለፁ፡፡
    የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳት ዶ.ር ኡባህ አደም በበኩላቸዉ ተቋሞቹ ከዚህ ቀደምም በቅንጅት የሚሰሩትን ስራዎች ይበልጥ ዉጤት በሚያመጣ መልኩ የላቸዉን ሀብት በይበልጥ እየተደጋገፉ በመጠቀም የተሻለ ዉጤት ለማምጣት ታስቦ የተዘጋጀዉ የጋራ መግባቢያ ፊርማ ሰነድ የሚደጋገፉበትን መስኮች ለይቶ ያሰቀመጠ መሆኑ የጋራ መግባቢያዉ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል ፡፡
    የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በበጎ ገፅታ ግንባታ እና በኮሙኒኬሽን መስክ የድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ በተሻለ ለመደገፍ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዉ በበኩሉ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በአቅም ግንባታዉ ዘርፍ በተሸለ ለመደገፍ የሚያስችል መሆኑ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልፆዋል፡፡