ኤጀንሲው ባዲሱ የመሬት ይዞታ አመዘጋገብና ሰነድ አያያዝ ላይ ከከተማው ለተውጣጡ 60 ስራ አጥ ወጣቶች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቁዋል፡፡
በከተማችን ረጅም አመታትን ከተሸገሩና ለማህበረሰብ ሮሮ ከተጋለጡ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የአስተዳደሩ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አሰራሩን በማዘመን ቅሬታዎችን በዘለቄታዊነት ለመፍታት የተለያ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ከስራዎቹ መሀል አንዱ የሆነውና በተቋሙ የመሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በቅርቡ እየተተገበረ የሚገኘው የይዞታ ማረጋገጥ ስራ በቅርቡ ከከተማዋ በተውጣጡና ስራ አጥ በነበሩ ወጣቶች ሊሰራ ከሰሞኑ 60 ለሚሆኑት ወጣቶች የ15 ቀን ስልጠናን በመስጠት ወደ ትግበራ ለመግባት በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ በኤጀንሲው የከተማ መሬት ምዝገባ መረጃ ኤገንሲ የስልታዊ ዘዴ ይዞታ ማረጋገጥ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የኃላፊው ተወካይ አቶ ሙአዝ ሀሰን ተናግረዋል፡፡
እንደ አቶ ሙአዝ ገለፃ በዚህ ስራ በተለይ በማህበረሰቡ ዘንድ ከይዞታ ጋር ተያይዞ ይስተዋሉ የነበሩ ቅሬታዎችን መፍትሄ ያገኛሉ ነው ያሉት፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎንም በከተማዋ ስራ አጥተው የተቀመጡ ወጣቶችን ስራ እድል ሚፈጥር ነውም ብለዋል፡፡
የአመራረጥ ሂደቱም ከቀበሌ02 ጋር በቅንጅት መሰራቱን የተናገሩት ተወካዩ በቀጣይም ወጣቶቹ ወደስራ ሲገቡ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ይደረግላቸዋልም ብለዋል፡፡
በስልጠናው ተካፋይ የሆኑ ወጣቶች በበኩላቸው ስልጠናው በቂ ክህሎትን ያስጨበጣቸው ስለመሆኑ ጠቁመው በዘሁም የስራ እድል ስለተፈጠረላቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡


