በድሬዳዋ አስተዳደር 15ተኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ምክኒያት በማድረግ በምድር ባቡር ስፖርት ሜዳ ዛሬ መካሄድ በጀመረዉ የንግድ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ የመክፈቺያ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት “እኩልነትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ለ15ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘዉ ይህ በዓል በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም ሃይማኖቶች እኩልነት በህግ ማዕቀፍ የተከበረበት መሆኑን አብራርተዉ ሁሉም የድሬ ደዋን የኢንደስቲሪ ከተማነት የነበራትን ህዳሴ እዉን ለማድረግ የበኩላቹሁን ድርሻ እንድታበረክቱ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ የድሬዳዋ ከንቲባ አህመድ ቡህ ፣ ምትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንደስቲሪና ኢነቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ከዲር ጁሃር ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ተገኝተዉ ባዛሩን ጎብኝተዋል፡፡


