የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ትኩረት በመስጠት የተሻለች ኢትዮጵያ መፍጠር በሚቻልበት መንገድ ሁሉም ሊረባረብበት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

    በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆጃቸው ያጡ ህፃናት ማህበረሰቡ ሊደግፋቸው ይገባል ሲሉ የድሬ ዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ሠራተኞች ለህጻናቱ ማሳደግያ ማዕከል እና ለትምህርት ቢሮ የትምህርት መርጃ መሳሪያና ለህጻናቱ ደግሞ የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳ ቁስ ድጋፍ አበረከቱ፡፡
    በድጋፍ መስጠት ስነ-ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ እንዳሉት የሀገር ግንባታ ከታች ይጀምራል እነኝህ በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆጃቸውን ያጡ ህጻናት የነገ ተስፋ ናቸው ስለዚህ ሁሉም በአቅሙ ቢረዳ ባለችን ትረፍ ጊዜ ከእነሱ ጋር ጊዜ ብናሳልፍ በትክክለኛ የእድገት ጎዳና ላይ እንዲሆኑ ማድረግ መቻል አለብን ብለዋል፡፡
    ድጋፉን የተረከቡት የሴቶችና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ከሪማ አሊ በበኩላቸው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሠራተኞቹ በራሳቸው ተነሳሽነት እንደዚህ ዓይነቱ ድጋፍ ማድረጋቸውን የሚበረታታና ለሌሎቹ የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች በአቅማቸው በተለያዩ ምክንያት ወላጆጃቸውን ያጡ አነኚህ ህጻናትን መደገፍ መቻል አለባቸው ብለዋል፡፡
    ሠራተኞች አሁን ያደረጉት ድጋፍ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን የአሁኑ ድጋፍ 15 ሺ ብር የሚገመት የምግብና የህጻናት ዳይፐር እንደሆነ እና ለወደፊትም እንደዚህ ዓይነት ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ያስታወቁት፡፡