የድሬደዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰራተኞች ዛሬ ባካሄዱት የ16ቱ ቀናት የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ አስመልክተዉ ባካሄዱት ፓናል ዉይይትን በንግግር የከፈቱት የድሬደዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አቶ ሸምሱዲን አምን እንደገለፁት ፆታዊ ጥቃት እንዲቆም በኮሙኒኬሽን ዘርፍ በህብረተሰቡ ግንዛቤ ዙሪያ በትኩረት ሊሰራ የገባል ብለዋል፡፡
በዓለማቀፍ ደረጃ ለ 29 ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጲያ ለ 15 ጊዜ ” ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን የማይታገስ ትውልድን በጋራ እንፍጠር! ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘዉን የዘንድሮ የ16ቱ ቀናት የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ በፓናል ዉይይት ያከበሩት የድሬደዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰራተኞች ዛሬ ባካሄዱት ዉይይት በዚህ የፓናል ዉይይት ላይ የ16ቱ ቀናት የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ታሪካዊ ዳራ ፣ በአሁኑ ወቅት በተለይም ከኮሮና በሽታ መከሰት ጋር ተያይዞ የፆታዊ ጥቃት ሁኔታ በዓለማቀፍ ደረጃ ፣ በሀገራችን ኢትዮጲያ እና በአስተዳደራችን ድሬ ደዋ ከተማ ያለበት ተጨባጭ ሁኔታ የተመለከተ ፁኁፍ ቀርቦ ዉይይት ተካሄዶበታል፡፡


