በድሬዳዋ አስተዳደር ከቢዮ አዋሌ ፣ዋሂል እና አሰሊሶ ገጠር ቀበሌዎች የተውጣጡ ባለድሻ አካላት የህገ ወጥ ስደትን በመከላከል እና የኤች አይቪ ኤድስ ዙሪያ እየተስተዋለ ያለውን መዘናጋት በንቃት እንዲታገሉ አላማ ያነገበው ስልጠና ዘርፈ ብዙ ግብአቶች እየተገኙበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በከተማ የጀመረው ስልጠና በገጠር ሲቀጥል የገጠሩ ማህበረሰብ እራሱን ህግ ወጥ በሆነ ችግር ውስጥ ከመክተት እና ለከፍተኛ አደጋ ከሚያጋልጡ መሰል ፈተናዎች እራሱን ማራቅ እንደሚገባው የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ የገጠሩ የንቅናቄ መድረክ በመክፈቻ ንግግር በከፈቱበት ወቅት አሳበዋል፡፡
ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት የጀርባ አጥንት የሆነው የገጠሩ ማህበረሰብ የህገ ወጥ ስደት እና ከኤች አይቪ ኤድስ ቀውስ ለመከላከል በንቃት መንቀሳቀስ እንዳለበት ተገልጻል፡፡
ለዚህም ይረዳ ዘንድ ይህ ስልጠና አጋዥ እንዲሆን የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይም መሰል እና የሀገር እና የማህበረሰቡን እድገት የሚፈታተኑ ቀውሶችን ለመከላከል ኮሚሽኑ በገጠርና በከተማ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ያለውን ቁርጠኛነት ተናግረዋል፡፡


