በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የውይይትና የደም ልገሳ አካሄዱ::

    በተካሄደው የውይይት መድረኩ 150 በላይ የትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ የኢትዮጵያ ባህል የሆነውን ይቅርታ ባይነትን በመተግበር የተፈጠረው ቁርሾ ሊወገድ እንደሚገባ ተገልጿል።
    ለውጥን መደገፍም ሆነ መተግበር በህግ መሆን እንዳለበትና
    ከታሪክ መማር እንጂ መጫረስ አግባብነት የሌለው በመሆኑ የታሪክና የባህል ልዩነት ሳይኖር የህዝብ ጥያቄ ሌላ ሆኖ እያለ የፖለቲካ ፍጆታና መሳሪያ መሆን ባህላችን አይደለም ተብሏል።
    ጥላቻን፣ ስድብን፣ ፍራቻን እና የውሸት ትርክት ለማንም የማይበጅ በመሆኑ ሚዛናዊና ህብረብሄራዊ መሆን ይገባል ነው የተባለው።
    መንግስት የወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃና ህገ መንግስቱን የማዳን እንጂ አንድን ብሄር ወይም አካባቢ ለማጥቃት አለመሆኑን ከመድረኩ ተገልጿል።
    ከተሳታፊዎች እንደ ድሬዳዋ ትግራይ ተወላጆች ወቅታዊ ሁኔታን በመረዳት ከመንግስት ጎን ነን፣ በወንድማማቾች መካከል የተፈጠረው ጦርነት የጭራሽ የማይደገፍና ሊሆንም የማይገባው ነበር፣ የሀገሪቷን ብልጽግና እውን ለማድረግ ሁሉም መረባረብ ይኖርበታል፣ በድሬዳዋ ነዋሪ የሆንነው የትግራይ ተወላጆችን መጠራጠር አግባብነት ስለሌለው ሊስተካከል ይገባል፣ ህወሃት አንድ ቡድን እንጂ ሁሉንም ትግራይ ተወላጆች የሚወክሉ አይደሉም፣ ብልጽግናን የማይወዱና የማይደግፉ ቡድኖቹ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው እንጂ የትግራይ ተወላጆች ብልጽግናን አይጠሉም፣ ካለፈው ታሪክ ተምረን ልናስቆመው ይገባል፣ በድሬዳዋ ትግራይ ተወላጆች የብልጽግና አባል በመሆናቸው በቀጣይ አደረጃጀቱ ጠርቶ ወደ ስራ መገባት አለበት የሚል አስተያየት ቀርበዋል።
    በመጨረሻም ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የማጠቃለያ ሀሳብ ተሰጥቶበታል።
    ከውይይቱ ጎንለጎን በተወያዮቹ ለመከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ መርሃግብር ተካሂዷል።