ከ49 ሺህ በላይ ዜጎች ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑ ተገለጸ፡፡

    የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት በሀገራችን ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረ ሲሆን በተለያዩ ክልሎች ተግባራዊ በመሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ያለ ፕሮግራም ሲሆን እስካሁንም ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት እያገኙ ነው።
    የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ትገበራን ለመጀመር የተለያዩ የዝግጅት ምዕራፎችን አጠናቆ ለአባላት የህክምና አገልግሎት ሊጀምር ነው፡፡
    የማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስትና የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች፣ የከተማ ቀበሌዎችና የገጠር ክላስተር አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው በአስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
    በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እንደተናገሩት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት እንኳን እንደ እኛ በማደግ ላይ ያሉት ሀገራትን ትተን ያደጉት ሀገራትም ይህንን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ትልቅ ጥቅም እያስገኘላቸው ይገኛል ብለዋል፡፡ አክሎም ም/ከንቲባው ይህንን የተጀመረው የጤና መድህን በአስተዳደራችንም በሀገራቸንም የማስቀጠልና ህብረተሰቡ የመድኑ ተጠቃሚ የሚያደረጉ ሰፋፊ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል፡፡
    በማስጀመሪያ መድረኩ የመሩት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በአስተዳደራችንም በቅርቡ አስተዳደሩ በመደበው 2 ሚሊዮን ብርና ሴቭ ዘ ቺልድረን የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ባደረገው ድጋፍ ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ላላቸው የአስተዳደራችን ነዋሪዎች የአባልነት ክፍያ ተከፍሎላቸው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስራዎች መጠናቀቃቸውን ሀላፊዋ ገልፀው በቀጣይ በራስ ፍላጎት የሚደረግ የአባላት ምዝገባን ለማጠናከር ቢሮው የተለያዩ የግንዛቤ ስራዎችን እንደሚሰራ አሳውቀዋል።
    በመድረኩ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አስተባባሪ ሲ/ር ሜሪ አምዴ እንዳሉት አንድ የቤተሰብ አባል በከተማ 520 ብርና በገጠር 250 ብር ክፍያን በመክፈል አመቱን ሙሉ ከቢሮው ጋር ውል ከገቡ የጤና ተቋማት የጤና አገልግሎትን ማግኘት የሚችሉበት ይህ ስርዓት ዜጎችን ከድንገተኛ ወጪ የሚታደግ፣ የህክምና አገልግሎት ጥራትን የሚጨምርና ሌሎችም በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ ህብረተሰቡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን በየቀበሌው የሚመዘገብበት ስርአትም መዘርጋቱን ገልፀዋል።
    የመድረኩ ተሳታፊዎችም የጤና መድኑ በተለይም የደሃ ደሃ ቤተሰቦች የጤና አገልግሎት በተገቢው እንዲያገኙ የሚያስችል በመሆኑ እንደ አስተዳደር አሁን ከታሰበው ቁጥር በላይ በአጭር ጊዜ ወስጥ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡
    በመስግያው ላይ የመስግያ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊና የአስተዳደሩ የጤና መድን ቦርድ አባል የሆኑት አቶ እዝቅያስ ታፈሰ እንደተናገሩት ይህንን የጤና በመድን አንደ ሀገር ከተጀመረ ጊዜ በአስተዳደራችን በተለያዩ ጊዜያት የአመራር ቁርጠኝነት መነሰና እስከ ዛሬ እየተጓተት በመምጣቱ ከአሁን በኋላ ግን በቀጥታ የማህበረሰብ የጤና መድኑ ሥራ ይጀመራል ይህንንም የሀገራችን የጤና ፖሊስ ለማስተግበረ ይረዳል ብለዋል፡፡
    በመድረክ መዝግያው ላይ የአለም ህፃናት አድን ድርጅት(save the children) አስተዳደሩ ማህበረሰብ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት ጀምሮ እስከ አሁን የጤና መድኑ የመክፍል አቅም የለላቸው ቤተሰቦች ለአንድ አመት የጤና መድን በመክፍል ትልቅ አስተዋጾ በማደረጉ የምስጋና ሰርተፊኬት ለድርጅቱ ተወካይ ተበርክቷል፡፡