የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተገልጋዩን ቁጥር ለማሳደግና የአገልግሎት ክፍያ ስርዓቱን ለማዘመን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደስራ መግባቱን ገለጸ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አግልግሎት ነዋሪው የሚያገኘውን አገልግሎት ጥራት በማሻሻል የተገልጋዩን ቁጥር ለማሳደግ ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የተቋሙ ዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ቴክኒካል ሰፖርት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ወ/ገብርኤል ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እንዳስረዱት በድሬዳዋ 45,000 (አርባ አምስት ሺህ) የሚሆኑ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ያላቸው ህጋዊ ተገልጋዮች መኖራቸውን ጠቁመው ሌላው ነዋሪ በህገ-ወጥ መንገድ የመብራት ቆጣሪ ካላቸው ተገልጋዮች…


