በድሬዳዋ ሳቢያን ኃይስኩል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የተሰራው ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ የእግር ኳስ መጫወቻ የአርቴቪሻል ሳር ሜዳ በዛሬው ዕለት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ በአቶ ከድር ጁሃር እና በኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ ተመርቋል ፡፡
*በማህበር የተደራጅ ወጣቶች የሰሩት የአርቴቪሻል እግር ኳስ መጫወቻ ሜዳው የሚያሰፈልገው ግብዓት ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ አስተዳደሩ ድጋፍ ማድረጉን *የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሃር ገልፀዋል ፡፡” በተለይ በዚህ ዘርፍ ላይ ወጣቶች መሰማራታቸው የስራ እድል ከመፍጠር አኳያም የሚያበረታታ እንደሆነ ም/ከንቲባው አቶ ከድር ጁሃር ተናግረዋል፡፡ ይህም ወጣቶች ለስፖርት ያላቸውን ፍቅር አንዱ ማሳያ ነው ሲሉም ገልፀዋል ፡፡”
*የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሻኪር አህመድ በበኩላቸው “የአርቴቪሻል ሳር ሜዳው ለአገልግሎት መብቃቱ ደግሞ ሌሎች ወጣቶች ከዚህ በመነሳት ልምድ ሊወስዱበት እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን ይህም ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ አለው ሲሉም ኮሚሽነር ሻኪር አብራርተዋል ፡፡ በዚህም የማዘውተሪያ ስፍራዎች ከማስፋፋት አንፃር ፡ የተደራጁ ወጣቶች በሜዳው ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ መኖሩን እና ለከተማው ውበትም የራሱ ሚና አለው ብለዋል፡፡ ” በቀጣይ በስፖርቱ ዘርፍ ለሚሰማሩ አካላት የኮሚሽኑ ድጋፍ እንደማይለይም ገልፀዋል ፡፡
* ድሬ ሜዳ ማህበር ሜዳውን አሰርቶ ለአገልግሎት አብቅቷል ፡፡ ይህ የእግር ኳስ የአርቴቪሻል ሳር ሜዳው 50 በ25ሜትር ስፋት እንዳለው የድሬ ማህበር አመራር ወጣት ጉይቶም ፍተዊ ተናግሯል ፡፡ አያይዞም ለመጫወቻ ሜዳውን ግንባታ በአጠቃላይ 1 ሚሊዮን 8 መቶ ሺህ ብር ወጪ እንደወጣበት ወጣት ጉይቶም ገልጿል ፡፡
*እንደ ድሬዳዋ ይህንን አይነት ዘመናዊ የአርቴቪሻል ሳር መጫወቻ 3 ሜዳ በማህበራት ሊሰሩ ችለዋል፡፡
ምንጭ ድሬደዋ ሰፖርት ኮሚሽን


