የአካባቢያቸውን ሰላም ከማረጋገጥ ባለፈ የነዋሪዎችን አንድነትና አብሮነት የሚያጎለብቱ ስራዎች በቀጣይ እንደሚሰሩ በ 08 ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ።

    ከዚህ ቀደም በ08 ቀበሌ ይከሰቱ የነበሩ ሁከትና ግጭቶችን በመፍታት በአካባቢው በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤት ሊገኝ ተችሏል፡፡
    በቀበሌው የሚገኙ ወጣቶች በራሳቸው ተነሳሽነት እያደረጉት ካለው የሮንድ ጥበቃ ስራ ባሻገር ከቀበሌ እና ከቀጠናው ፖሊስ አመራርና አባላት ጋር በመሆን በቤተ-እምነቶች የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል።
    የቀበሌው ነዋሪዎችና ወጣቶች በጋራ የሮንድ ጥበቃ ላይ ተሳታፊ በመሆን የአካባቢያቸውን ሰላም ከማስጠበቃቸው ባለፈ በፅዳት ዘመቻ ላይም ተሳታፊ በመሆን ላይ ለሚገኙ ከ 100 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ ምችችት በማድረግ በስራ እድል ፈጠራው ተጠቃሚ ለማድረግ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ የቀበሌው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አዩብ አብዲ ተናግረዋል፡፡
    በ 08 ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ከቀጠናው ፖሊስ ጣቢያ አመራርና አባላት ጋር በመሆን በቀበሌው በሚገኙ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን እና በሼክ አብዱረህማን ዳሞታ መስኪድ በመገኝተው የፅዳት ዘመቻውን ያደረጉ ሲሆን በዚሁ የፅዳት ዘመቻ ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በበኩላቸው የፅዳት ዘመቻው ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው ከመደሰታቸውም ባለፈ የአካባቢው ነዋሪዎችን አንድነትና አብሮነት የሚያጎላ በመሆኑ ይህንኑ ተግባር በቀጣይም አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተናግዋል፡፡