የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ “ጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግበዓት ቁጥጥር የሥራ ሂደት መሪ” ሲስተር ሰሪዶ ዑመር አማካኝነት በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ በድሬዳዋ የተሰሩ ስራዎች በሪፖርት መልክ አቅርቧል፡፡
በቀረበው ሪፖርት መሰረት በሀገራችን የትምባሆ ቁጥጥር ምን እንሚመስል እና ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ ያጋጠማቸውን ተግዳሮቶች ፣ ከህብረተሰቡና ከመንግስት የሚጠበቁ ኃላፊነቶች በተጨማሪም ትንባሆን ለመከላከል በወጣው አዋጅ ዙሪያ ውይይት ተደረጓል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች ከጤና ቢሮ፣ ከመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ፣ ከድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ፣ከፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ፣ ከፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎችም ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡


