4ተኛው ሀገር አቀፍ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በድሬዳዋ ተካሄደ

    4ተኛው ሀገር አቀፍ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን “ከጳጉሜ እስከ ጳጉሜ እንደርሳለን” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ተካሄደ።
    የኢፌድሪ የትራንስፖርት ሚኒስተር ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በስነ ስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደተናገሩት በሀገር አቀፍ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ቀን በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞችም በተመሳሳይ እንደሚካሄድ በመጠቆም በዛሬው እለት በድሬደዋ 4ኛውን የሞተር አልባ(ብስክሌት)ስናከብር ድሬደዋ ቀደም ሲል ከሞተር አልባ ጋር ያላትን ታሪካዊ ትስስር እንዲሁም የሞተር አልባ ስትራቴጅን ተግባራዊ ለማድረግ ከተመረጡ ከተሞች መካከል አንዷ በመሆኖ ነው ብለዋል ።
    ክብርት ሚኒስተሯ ከዚህም ጋር አያይዘው በኃገራችን ለእግረኞች የተለዪ መንገዶች ምቹ ባለመሆናቸው የብስክሌት ትራንስፖርት ተጠቃሚዋች ከሞተር ተሽከርካሪዋች ጋር በጋራ መንገዶችን በመጋራታቸው የብስክሌት ተጠቃሜዋች ቁጥር እንዲቀንስ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱን የድሬደዋ ከተማ አንዷ ማሳያ ናት ብለዋል።
    ይህንንና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ከተሞች በመሰረተ ልማት ትግበራዘቸው የእግረኞች እና የብስክሌት ተጠቃሚዋችን ከትራፌክ አደጋ የተጠበቀ እንዲሆን እንደ ሀገር የተቀመጠውን እቅድ በመተግበር ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት ስርአት እንዲኖር የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲወጡ ሲሉ ክብርት ሚኒስተሯ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
    የአስተዳደሩ ከኒትባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ በስነስርአቱ ላይ ባስተላለፍት መልዕክት እንደተናገሩት በድሬደዋ ከሞተር አልባ የትራንስፖርት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በየወሩ አንድ ጊዜ ማህበረሰቡ በአካባቢያቸው በማዘጋጀት
    አካላዊ ርቀቱን በመጠበቅና አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በየአካባቢው እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርቧል።
    ከትባው ከዚህም ጋር በማያያዝ ሁነቱ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን ከማስተዋወቁም በላይ ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ ያስችላል ብለዋል።
    በስነስርአቱ የአስተዳደሩ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስተርና ለድሬደዋ አስተዳደር ፣ለፖሊስ ኮሚሽንና ለመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ላሳዪት አጋርነት የምስጋና ስጦታ አበርክቷል።