በድሬዳዋ አስተዳደር የመልካ ጀብዱ ቀበሌ ነዋሪዎች የአካባቢያቸውን ሠላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ለአስተዳደሩ ሁለንተናዊ ልማት የድርሻቸውን ይወጡ ዘንድ ጥሪ ቀረበ።

    የመልካ ጀብዱ ቀበሌ /01 ቀበሌ ከድሬዳዋ አስተዳደር ግዙፍ የሀገር ፕሮጀክቶች የሚገኙበት ቀበሌ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በቡድኖች የሚቀሰቀሱ ጸቦች በቀበሌዋ ነዋሪዎች ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተግዳሮት ሆኗል።
    ይህንን ችግር በዘላቂነት በመቅረፍ የነዋሪውን ብሎም የአሥተዳደሩን ሠላምና ጸጥታ ለማሥጠበቅ ነዋሪዎቹ የእርቀ ሠላም ኮሚቴ ማቋቋሚያ ኮንፈረንሥ አካሂደዋል።
    በመድረኩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ፣ የድሬዳዋ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስና ኡጋዞች እንዲሁም አባገዳዎች ነዋሪው ለሠላምና ጸጥታው መከበር እጅለእጅ ተያይዞ ይሠራ ዘንድ መልዕክት አሥተላልፈዋል።
    ምንጭ:- ድሬ ብዙሃን መገናኛ