መጪው የጥምቀት በዓል ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል የጋራ የውይይት መድረክ ተካሄደ ::

    የውይይት መድረኩ የእምነት አባቶችና ፖሊስን ጨምሮ ሌሎች የፀጥታ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ነው በጋራ በዛሬው እለት የተካሄው ፡፡
    የውይይት መድረኩን የመሩት የድሬዳዋ ፍ/ፀ/ህ/ጉዳዮች ቢሮ
    ሀላፊ አቶ ሙሳ ጣሀ እንደተናገሩት በእምነቱ ተከታዩች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በአል የሌሎች እምነት ተከታዩች ጭምር በወንድማማችነት አብረው የሚያከብሩት ትልቅ በዓል እንደመሆኑ በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ በፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት እንደተደረገ ጠቁመው የሀይማኖት አባቶችም ለበአሉ በሠላም መከበር ያላቸው ሚና ከሁሉ የላቀ በመሆኑ የጋር ውይይት መደረክ ሊካሄድ ችሏል ብለዋል፡፡
    የድሬዳዋ ፖሊሰ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሀላፊ ምትል ኮሚሽነር ጉሌድ ድርዬ በበኩላቸው በሀይማኖቱ ስርአት መሰረት ሠላማዊ ሆነ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል የሀይማኖቱ መሪዎችና ህዝበ ምእመኑ እንደ ከዚሂ ቀደሙ ሁሉ የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል::
    በጋራ የውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉት የሀይማኖት አባቶችና ተወካዮች በበኩላቸው ከሁሉም ሰው ጋር በሠላም መኖር የእምነቱ መርህ እንደመሆኑ በዓሉ ትክክለኛ የእምነት መርህ ይዞ እንዲከበር ለማድረግ የበኩላቸውን ሀላፊነት ሁሉ እንደሚወጡ ተናግረዋል::
    በዚሁ የጋራ የውይይት መድረክ የሀይማኖት አባቶችና ተወካዮች እንዲሁም ፖሊስን ጨምሮ ሌሎች የፀጥታ ተቋማት አመራሮችና ተወካዮች ተገኝተዋል::
    ምንጭ ፡ ድሬ ፖሊስ