በተፈጠረልን ግንዛቤ ጤናችንን በአከባቢያችንን ንፅህና ለመጠበቅ ሜዳ ላይ መፀዳዳትን ለማስቀረት በትኩረት እየሰሩ መሆኑን ተናገሩ ፡፡

    የአካባቢ ጽዳት በማስጠበቅ ህብረተሰቡን ከተለያዩ በሽታዎች ለመከላከል እና ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ አካባቢን የመፍጠር ስራ እተሰራባቸዉ ካሉ 6 ገጠር ቀበሌዎች አንዱ በሆነዉ የቢዮ አዋሌ ገጠር ቀበሌ ሁሉም አባወራ የመፀዳጃ ቤት እንዲኖረዉ ለማድረግ በቀበሌዉ የመፀዳጃ ቤት ጉርጓድ ቁፋሮና ቤት ግንባታ ያለበትን ሁኔታ ተዘዋውረን በተመለከትንበት ወቅት ካነጋገርናቸዉ የቢዮ አዋሌ ገጠር ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሰኣዳ ኡሶ እንደገለፁት የማንኛዉም ልማት መሰረት ጤና መሆኑን ገልፀዉ ጤናችንን በጽዳት ለመጠበቅ እና ሜዳ ላይ መፀዳዳትን ለማስቀረት ሁሉም የቀበሌው አባወራ መፀዳጃ ቤት ሊኖረው እንደሚገባ ተግባብተን ወደ ስራ መግባታቸዉንና ስራዉ ጥሩ እየሄደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
    የቢዮ አዋሌ ገጠር ቀበሌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ጀማል በበኩላቸዉ እንዳሉት የቢዮ አዋሌ ገጠር ቀበሌ 15 መንደሮች እና 1700 አባወራዎች ያሉት መሆኑንና ከነዚህ አባወራዎች 300 አባወራዎች ከዚህ ቀደም ሰርተዉ በመፀዳጃ ቤት እየተጠቀሙ ከሚገኙት ዉጪ የቀሩት 1400 አባወራዎች በዚህ የንቅናቄ ስራ እንዲኖራቸዉ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑንና እስካሁን ሁሉም የጉርጓድ ቁፋሮ ስራን በማጠናቀቅ ወደ ቤት ግንባታ መግባታቸውን አብራርተዋል፡፡