የድሬዳዋ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ በዛሬው እለት <ምክንያታዊ ወጣት እንፍጠር>>በሚል መሪ ውይይት አካሄደ ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን እቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የድሬዳዋ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ አደረጃጀት<<ምክንያታዊ ወጣት እንፍጠር>>በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የውይይት መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እንደተናገሩት ወጣቱ መሰረታቸው ያልታወቁ መረጃዎችን ሳይከተል እንዲሁም ሁኔታዎችን ሲደግፍም ሆነ ሲቃወም ምክንያታዊ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። የምክንያታዊ ወጣቶች ንግግርና ሙግት በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት አቶ አለማየሁ…


