በድሬደዋ የቀበሌ 05 ነዋሪዎች ከቀጠናው ፖሊስ ጋር በመሆን የጥምቀት በአል በሚከበርበት ስፍራ የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ::

    ነዋሪዎቹ ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት ሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል::
    በአሉ በሚከበርበት ስፍራ ተገኝተው የፅዳት ዘመቻውን ያደረጉ ነዋሪዎች እንደገለፁት በአልን ተንተርሶ ግጭት ለማስነሳት የሚፈልጉ ሀይሎች ያሰቡት እኩይ አላማ እንደማይሳካ ብሎም በአሉ በአብሮነትና በአንድነት የሚከበር መሆኑን ጭምር ለማሳየት በማሰብ የፅዳት ዘመቻውን ማድረጋቸውን ገልፅፕው ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል::
    በዚሁ የፅዳት ዘመቻ ላይ የኦርቶዶክስና እስልምና እምነት አባቶች ተገኝተው በፅዳት ዘመቻው ላይ ለተገኙ የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎች መልእክት በማስተላለፍ ቡራኬን ሰተዋል::
    የፅዳት ዘመቻው የድ/ዳ/አስ ፍ/ፀ/ህ/ጉዳዮች ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ አብደላ በከር በተገኙበት የ05 ቀበሌ የተለያዩ መንደሮች የሚገኙ የተለያየ እምነት ተከታይ የሆኑ ነዋሪዎችና የእምነት አባቶች ፣የ05 የቀበሌና የአዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ አመራር እና አባላት ተከናውኗል::
    የመረጃው ምንጭ ድሬ ፖሊስ