የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ሙራድ በደዊ እንደገለፁት ጽ/ቤቱ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በቀጣይ ለመስራት የሚያስችሉ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ በርካታ የጥናት እና የምርምር ስራዎችን ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡
የጥናት ስራዎቹም በቱሪዝም ስራ እድል ፈጠራ፣በአፈረን-ቀሎ የኪነ-ጥበብ ቡድን እንዲሁም ኡጋዛዊ የግጭት አፈታት ሥነ-ሥርዓት በተለይም ባህላዊ የኢሳና ጉርጉራ የግጭት አፈታት ላይ በተመለከተ የጥናት ስራዎች ያተኮረባቸው እንደሆኑ ገልፀው የጥናቱ ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት በዚህ በጀት አመት ወደ ስራ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰለሞን እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ ምርምር በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው።
በተለይም የህብረተሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናት ስራዎች ላይ በትኩረት ዩኒቨርሲቲ በመስራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር የስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙ ሲሆን በቀጣይ ስራዎች በጥራት ለመስራት ያስችል ዘንድ አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
ዶ/ር ሰለሞን ከዚህም ጋር አያይዘው በአስተዳደሩ በቱሪዝሙ ዘርፍ የሚታየውን የስራ አጥ ዜጎችንም ክፍተት ለመሙላትም የጥናት ስራው ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው ዩኒቨርሲቲውም ከአካባቢው ማህበረሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎች ከሌሎች ሴክተር ተቋማት ጋር በመቀናጀትም ዩኒቨርሲቲው በመስራት ላይ መሆኑን አቶ ሰለሞን ጨምረው ገልፀዋል ።


